የፊልሙ ጭብጥ
ሀገሩን ከጠላት ለመጠበቅ ህዝብን ለማገልገል ወታደር ሆኖ የሚያገለግል ደሳለኝ የሚባል ሰው አስተማሪ ከሆነችው ከሚስቱ ህይወት ጋር በፍቅር አንድ ልጅ ወልደው ሲኖሩ የኢትዮ ሶማሌ ጦርነት ላይ ድንበር ለማስጠበቅ ወደ ጦር ግንባር የሄደው ደሳለኝ ድል አድርጎ ሲመለስ የልጁና የሚስቱን ናፍቆት ሳይወጣለት ልጁ በድንገት ለጫወታ ባነሳው የአባቱ ሽጉጥ የገዛ አባቱ ላይ ተኩሶ ይገለዋል፡፡ ከዛች መጥፎ አጋጣሚ በኃላ የልጁ እናት በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ትወድቃለች ልጇን ትጠላለች በየቀኑ ትጠጣለች በመምህርነት ስራዋ ላይ ከፍተኛ ተፅኖ ውስጥ ትወድቃለች ፡፡ከግዜ በኃላ አንድ ድንገተኛ ሰው ቤቷ ህይወቷ ውስጥ መጥቶ ልጇን ይቅር እንድትለው እና 97 ሰው አስታርቆ 98ኛ እንደሆነች እንዲሁም መቶ ሰው ለማስታረቅ አላማ እንዳለው ይነግራታል ከብዙ ድካምና ቻሌንጅ በኃላ ህይወት ይቅርታ ማድረግ ገብቷት ልጇን ይቅርታ አድርጋለት ወደቀድሞ ማንነቷ ትመለሳለች ፡፡
እንግዲህ በዋናነት የፊልሙ ጭብጥ ይቅርታ በህይወታችን ሌላ ማንነት እንዲፈጥር ማድረግ እና ምን ያህል ሰው ይቅርታ ለማድረግ እናስባለን ካላሰብንም በሂወታችን ይቅርታ ለማለት እናስብ የሚል ነው በመሆኑም በጥበብ መንገድ ይቅር እንባባል የሚል መልእክት ይዟል ፡፡